Home iconደብርና በዓል
ChurchesFeastsSearchLogin

Church Directory

Find churches in our directory

Tsedenya smegn kidist maryam gedam
Tsedenya smegn kidist maryam gedam
Burayu Maryam

ደብሩ ፄዴንያ ስመኝ ቅድስት ማርያም ትባላለች በቡራዩ ከተማ የምትገኝ ስህን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፣ የሐዋርያዉ ናትናኤል ታቦታት ይገኙበታል ። በዋናነት መስከረም ፲ የንግስ በአል ሲሆን ሌሎች የእመቤታችን በአላት ና የሐዋርያዉ ናትናኤል በአሎችም ይከበራሉ። 38 አመታትን አስቆጠረ ፍኖተ ብርሃን የተሰኘ ሰንበት ትምህርት ቤት አላት። ገዳም እንደመሆኗ መጠን መነኮሳት ይገኙባታል እንዲሁም የገዳማዊ ስርዓቶችም ይደረጉባታል ።

View Details
kechene debreselam and debretiguhan medhanialem and st gebriel
kechene debreselam and debretiguhan medhanialem and st gebriel
kechene

ቀጨኔ ደብረሰላምና ደብረትጉሃን መድሃኒአለም በልጅ እያሱ ጊዜ የተመሰረተ ደብር ነው።

View Details
st giorgis
st giorgis
piaza, addis ababa, ethiopia

አዲሱ ቤተ ክርስቲያን የተገነባው ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ፍርስራሽ ላይ ነው። በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የተሰየመው የቤተክርስቲያኑ ታቦት (ታቦት) ከጣሊያኖች ጋር በተደረገው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያውያን ድል ባደረጉበት ወቅት ነው።[2]። ከመስራቾቹ አንዱ አንዳርጋዬ ሲሆን ልጃቸው ክሰላ አንዳርጋዬ እና ባለቤታቸው አጎናፍር ወልደየስ የተቀበሩት በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው። ሕንጻው በ1938 ዓ.ም በጣሊያን የቱሪስት እትም ላይ የአውሮፓ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ንድፍ አተረጓጎም ጥሩ ምሳሌ እንደሆነ ተገልጿል[3]። በ1937 የኢጣሊያ ፋሽስት ባለስልጣናት ሕንፃውን አቃጥለውታል።ካቴድራሉ በ1941 ዓ.ም ከነጻነት በኋላ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ታደሰ።

View Details
መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
ፒያሳ,አዲስ አበባ

ዐድዋን ጨምሮ በተለያዩ ጦርነቶች በመዝመትና በነገሥታት መናገሻነቱ የሚታወቀው ታሪካዊው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ባለዕዳ በሚያደርግና አገሪቱን በሚጎዳ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና የመልካም አስተዳደር ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ ደብሩ በራስ አገዝ ልማት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱ የደብሩ ሠራተኞችና ምእመናን በሰነድና በቃል ባቀረቧቸው አስረጅዎች፣ ‹‹በልማቱ በማመካኘት የሚታየው የሥራ ሒደት መልሶ ልማቱን የሚያኮላሽና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በተለይም ከ፳፻፮ ዓ.ም. መጀመሪያ አንሥቶ በደብሩ አስተዳደሪ መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ የሚፈጸሙት የመዋቅር ጥሰትና መመሪያን ያልጠበቁ ግለሰባዊ አሠራሮች በመባባስ ላይ እንዳሉ ነው ያስረዱት፡፡ ለዚኽም ከሕንፃ ግንባታና የኪራይ ውሎች ሕጋዊነት፣ ከኪራይ ገቢ አሰባሰብና ከወጪዎች አግባብነት አኳያ የደብሩ ገንዘብ አላግባብ እንዲባክን ተደርጓል ያሉባቸውን ጉዳዮች በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ደብሩ ‹‹ዳዊት ወንድሙ›› በተባለ የሕንፃ ሥራ ተቋራጭ በማሠራት ላይ የሚገኘው ባለአራት ፎቅ የንግድ ማዕከል ሕንፃ፣ በሰኔ ወር ፳፻፬ ዓ.ም. በውስን ጨረታ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት በሰበካ ጉባኤውና በልማት ኮሚቴው ጥምር የጋራ ስብሰባ ለአሸናፊው ድርጅት የተወሰነና የኮንትራት ውሉም በብር 61‚234‚885.02 ጠቅላላ ወጪ የተፈጸመ እንደነበር ተገልጧል፤ አማካሪ ድርጅቱ የተቀጠረውም በግልጽ አሠራር ተለይቶ ሲኾን በግንባታው ሒደትና በክፍያዎች አፈጻጸም የልማት ኮሚቴው ቴክኒክ ክፍል ሞያዊ ይኹንታና ማረጋገጫ በመስጠት ልማቱን ለማገዝ ጥረት አድርጎ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ውሉ እንደ ቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ በማዕከል (በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት) ተፈቅዶ ግንባታው እየተካሔደ ባለበት ኹኔታ፣ የደብሩ አስተዳደር በዲዛይን ክለሳ ሰበብ የግንባታ ዋጋውን ከዕጥፍ በላይ በማናር የሥራ ውሉን መቀየሩ ተመልክቷል፡፡ አልፋ አማካሪ መሐንዲሶች የተሰኘውን የቀድሞውን አማካሪ መሐንዲስ በማሰናበት ‹‹የዲዛይን ክለሳና ተያያዥ ሰነዶች ፍተሻ በማስፈለጉ›› በሚል ዳንኤል አሰፋ ፕራክቲሲንግ አርክቴክቸር የተባለ አማካሪ ያለምንም ግልጽ መመዘኛና ውድድር በጥር ወር መጀመሪያ ላይ ቀጥሯል፡፡ ከደብሩ ዋና ጸሐፊ ጋራ ባለው ግለሰባዊ ትውውቅ የመጣው አማካሪ መሐንዲስ ያለውድድር ለሠራው የፕላን ማሻሻያ ብር 80‚500 የተከፈለ ሲኾን የግንባታ ወጪውም ከብር 175 ሚልዮን በላይ እንዲንር መደረጉ ታውቋል፡፡ የኮንስትራክሽንን ሕጉን በመጣስ ያለጨረታ የተሰጠው ‹‹የፕላን ማሻሻያ›› እና የቃለ ዐዋዲውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሀገረ ስብከቱ ባልፈቀደው ‹‹የተከለሰ ዲዛይን›› መቀጠሉ የተገለጸው ግንባታ፣ በአነስተኛ ግምት ከብር 80 ሚልዮን ያላነሰ የወጪ ልዩነት ቢታይበትም እንደማሻሻያ የተጨመሩት የአሳንሰርና የኤሌክትሪክ ዝርጋታዎች የተጠቀሰውን ወጪ ምክንያታዊ ለማድረግ እንደማይበቁ ተገልጧል፡፡ ሕንፃው ከጠቅላላ ሥራው ከሢሦ ባልበለጠበት በአኹኑ ደረጃው እንዲከፈል የታዘዘው ወጪ ከብር 25‚536‚438.98 በላይ መድረሱ፣ ሥራው በማዕከል ከተፈቀደው ውጭና በተለየ ውል እየተካሔደ መኾኑን እንደሚያረጋግጥ በአስረጅነት ተጠቅሷል፤ የልማት ኮሚቴው ቴክኒክ ክፍል የግንባታ ጥራት ምስክርነት ያልተደመጠበትና የጋራ ውሳኔና ስምምነት ያላረፈበት በመኾኑም ለተቋራጩ ሲፈጸም የቆየው ክፍያ አግባብነት በገለልተኛ አማካሪ መረጋገጥ እንደሚገባው ተጠይቋል፡፡ በዲዛይን ክለሳ ስም ከ175 ሚልዮን በላይ የናረው የግንባታ ወጪ በተጋነነ ዋጋ በሚፈጸሙ የሥራ ውሎች አላግባብ እንዲባክን እየተደረገ ስላለው የደብሩ ገንዘብ ኹነኛ መገለጫና አስቸኳይ እርምት የሚያስፈልገው ነው የሚሉት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ደብሩን በጎበኙበት ጥር ወር አጋማሽ ግንባታው የሚጨርሰው ጠቅላላ ወጪ እንደኾነ ተደርጎ በሪፖርት እስከ መገለጽ መድረሱ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ ከሕንፃ ግንባታው በተጨማሪ በዕድሳትም ስም ወጪ የተደረገው እስከ ብር 60‚000 ከፍተኛ ገንዘብ ተገቢው የደረሰኝ ማስረጃ ሳይቀርብ እንዲወራረድ አስገዳጅ ትእዛዝ በአስተዳደሪው እንደሚሰጥ በአቤቱታ አቅራቢዎቹ ተብራርቷል፡፡ የደብሩ ይዞታዎች በኾኑ ኹለት ሕንፃዎች ላይ ቅርንጫፎችን ለመክፈት የደብሩ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ጋራ ያደረገው የኪራይ ውል የቃለ ዐዋዲውን ድንጋጌ የጣሰና ‹‹ሀገረ ስብከቱ ምን አገባው›› በሚል የተፈጸመ እንደኾነ ነው የደብሩ ሠራተኞች የሚያስረዱት፡፡ የደብሩ አስተዳደር መስከረም ፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከዲስትሪክቱ ጋራ በፈጸመው የዐሥር ዓመት የኪራይ ውል፣ የአቡነ ጴጥሮስ ቅርንጫፍ እና መሀል ፒያሳ ቅርንጫፍ ለመክፈት ብር 12 ሚልዮንና ብር 28 ሚልዮን በድምሩ ብር 40 ሚልዮን እንዲከፈለው መስማማቱ ታውቋል፡፡ አስተዳደሩ በውሉ መሠረት የኪራይ ክፍያው እንዲለቀቅለት ባንኩን የጠየቀ ከመኾኑም በላይ ስለቅድመ ክፍያው አፈጻጸም በጻፈው ደብዳቤ መሠረት እስከ አኹን ከብር 14 ሚልዮን ያላነሰ በቁጠባ ሒሳቡ ገቢ እንደተደረገለት ነው የተጠቆመው፡፡ በቃለ ዐዋዲው አንቀጽ 12(8) መሠረት፣ በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሳይፈቅዱና መመሪያ ሳይሰጡበት በተፈጸመው ውል የተገኘው ከፍተኛ ግምት ያለው የኪራይ ገንዘብ፣ መመሪያን ባልጠበቁ ከፍተኛ ክፍያዎች ሊባክን እንደሚችል አቤቱታ አቅራቢዎቹ ስጋት አላቸው፡፡ በዚህ ረገድ ለተቋራጭ መሐንዲሱና ለአማካሪው በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ብር ወጪ እየተደረገ መሰጠቱ የሚመለከታቸውን የሥራ ሓላፊዎች ማስጨነቁን ሠራተኞቹ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ተቋራጭ መሐንዲሱ ብድር ጠይቀዋል›› በሚል አራት ሚልዮን ብር በብድር መሰጠቱ በምሳሌነት ተወስቷል፡፡ ብድሩ ‹‹ለሥራው በጊዜ መፋጠን አስተዋፅኦ ስላለው›› በሚል የተፈቀደ ቢኾንም እንዲከፈል የታዘዘው ገንዘብ የሚመለስበት ዝርዝር ኹኔታ ሳይብራራና የሚመለከታቸው ክፍሎች ሐሳብ ሳይካተትበት እንደኾነ ተገልጧል፡፡ ለልማት መዋል የሚገባው የደብሩ ገንዘብ በብድር መልክ የተሰጠው ባለዕዳው ተቋራጭ፣ ደብሩ ከሚያከራያቸው ቤቶችና ቦታዎች ላይ ለጋራዥና ለመጋዘን ከተከራየበት ጊዜ ጀምሮ ከብር 420‚000 በላይ የኪራይ ውዝፍ ያለበትና ዕዳውን እንዲከፍል በተደጋጋሚ ቢጠይቅም በአስተዳደሩ በኩል የማስፈጸም ዳተኝነት መታየቱ ተዘግቧል፡፡ ይብሱኑ ተቋራጩ ከደብሩ በስተምሥራቅ በብር 12 ሚልዮን ብር ወጪ ይገነባል ለተባለው ሕንፃ ያለውድድር ለሠራው ፕላን ብር 35‚000 ተከፍሎታል፤ ፕላኑ በገለልተኛ ባለሞያ ባልተገመገመበትና የግንባታ ወጪ ዝርዝር ባልቀረበበት ኹኔታም የተባለውን ባለኹለት ፎቅ ሕንፃ እንዲሠራ ያለጨረታ የሥራ ውል ለመስጠት መታሰቡ ስጋታቸውን ከፍ እንዳደረገው ሠራተኞቹ አስረድተዋል፤ ባለዕዳነቱ ከመንግሥት ቫትም ጭምር እንደኾነ ነው አክለው የሚናገሩት፡፡

View Details
ሰገነት ቅድስት ኪዳነምህረት እና አቡነ ዜናማርቆስ ገዳም
ሰገነት ቅድስት ኪዳነምህረት እና አቡነ ዜናማርቆስ ገዳም
kechene

በ 2013 ዓ/ም በብጹአ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮፕያ ሊቀጳጳስ ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልካም ፈቃድ መስከረም 3 ተመሰረተች።

View Details
ደብረ ጽጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን
ደብረ ጽጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን
kassanchis, Addis Ababa

A beautiful and historical church. This place was built in 1875 (Ethiopian Calendar). A peaceful church as well. Saint Urael Church is one of the most iconic holy sites for Ethiopian Orthodox Church in Addis Ababa. I hope that the place will be a beautiful spot and get more attractions when the current city development project in this area completed by the city administration.

View Details